በጎርፍ የተወሰዱት እናት አስከሬን አልተገኘም ዘንድሮ ብቻ 41 ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ሞተዋል flash flooding killed 41 people died in Addis Ababa in this year alone
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በበኩላቸው፤ የወ/ሮ ፀዳለ አስከሬን ሊገኝ ያልቻለው ቤተሰብ በዕለቱ ባለማመልከቱ መሆኑን ገልፀው፣ ብዙ ጊዜ በጎርፍ የሚወሰዱ ሰዎች አስክሬን በሌላ አካባቢ ጎርፉ ሲተፋቸው እንደሚገኝና የወ/ሮ ፀዳለን አስክሬንም ለማግኘት ወንዙ የሚሄድበትን አቅጣጫ እየተከተሉ ፍለጋቸውን እያከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጎርፉ ራቅ ያለ አካባቢ ወስዶ ከጣላቸው በኋላ ቶሎ መገኘት ካልቻሉ አስከሬኑ በአውሬ የመበላት እድል እንደሚገጥመው ገልፀው፤ አብዛኛውን ጊዜ ግን የሚጠፋ አስክሬን እንደማይኖር ተናግረዋል፡፡ ዘንድሮ በጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች 41መሆናቸውን የገለፁት ባለሙያው፤ ባለፈው ዓመት 34 ሰዎች በጐርፍ ተወስደው መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡
sodere..
No comments:
Post a Comment