Thursday, November 7, 2013

ሂውማን ሄር በሴቶች ላይ የባዶነትን ስሜት ይፈጥራል


ከአስመረት ብስራት humman hair
ለውበት ሲባል የማይደረግ ነገር የለም። አንዳንድ ሰው በተፈጥሮ የተሰጠውን ውበት ተንከባክቦና አሳምሮ መጠቀም ሲፈልግ ሌላው ደግሞ ተጨማሪ ወይም ሰው ሰራሽ መጠቀ ሚያዎችን በመጨመር ለመዋብ ጥረት ሲያደርግ እናያለን። ሰው ሰራሽ መዋቢያን በመጨመር ከምንጠቀምባቸው የተፈጥሮ ፀጋዎቻችን አንዱ ደግሞ ፀጉር ነው።
ፀጉር ላይ እየተጨመሩ በሹሩባ መልክ የሚሰሩ ዊጎች ፤የሚሰፉና ሌሎች ሰውሰራሽ ዊጎችን በመጨመር ማሳመር ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ ከዘመኑ ጋር እያደገ በመጣ ቴክኖሎጂ የተነሳ የሰው ፀጉር በሚሰፋና በሚጣበቅ መልኩ እየተዘጋጀ ገበያ ላይ በብዛት ወጥቷል።
በአብዛኛው ከኤስያ አህጉር የሚመጣው የሰው ፀጉር «ሂውማን ሄር»ችግረኛ ሰዎች እንደ መተዳደሪያ የሚሸጡት መሆኑን ነው የሚነገረው። አንዳንዴም እርግጥ መሆኑ ብዙ ማስረጃ ቢጠይቅም በአምልኮ የተነሳ ፀጉርን መስዋእት ከሚደረግበት ስርአት የተሰበሰበ ነው ይባላል። እና ይህ የሰው ፀጉር ሃገራችን ገብቶ በብዙ ሺ ብሮች እየተሸጠ የሴቶች ውበትና አብዛኛዋን ሴት የረጅም ፀጉር ባለቤት አድር ጓል።
ይህ ፀጉር እንዴት እንደሚሰራ፤ያለው ጥቅምና ጉዳት ምን እንደሚመስል በሚሊንየም የውበት ሳሎን የፀጉር ባለሞያ የሆነች ወይዘሪት መሰረት ታደሰ(ኮች)ን አናግረናል።ሂውማን ሄር የተለያየ ርዝመትና አይነት አለው። ከ12 እስከ24 ኢንች በአብዛኛው የተለመደ ሲሆን የሷ ደንበኞች ግን 18 ኢንቹን እንደሚመርጡ ነግራናለች።
ይህን ፀጉር ለመሰራት ፀጉሩ ታጥቦ ፀድቶ ከታች ያለው የተፈጥሮ ፀጉር እንዳይጎዳ ማገገሚያ ቅባቶችን ከተቀባ በኋላ ሹሩባው ተሰርቶ ሂውማን ሄሩ ይሰፋል፡፡ በአብዛኛው ከፊት ያለው የተፈጥሮ ፀጉር ለመሸፈኛነት ቀርቶ ሁሌ ሰለሚሰራ የመሃልኛው ፀጉር እየጠነከረና እየፋፋ ሲሄድ ከፊት ያለው ደግሞ ሙቀት የሚያገኘው የፀጉር ክፍል እየሳሳ፣ እየተበጣጠሰና እየተጎዳ ይሄዳል።
ሂውማን ሄርን ቀለም መቀባትም ሆነ የፈለጉትን አይነት እስታይል ማስያዝ ይቻላል። እንደ ራስ ፀጉር መጠቀም እንደሚቻል የተናገረችው ኮች በየእለቱ በዚሁ ፀጉር የምትሰራ ሴት በአመት ሊያልቅባት የሚችል ሲሆን ለፕሮግራሞችና አልፎ አልፎ በቻ በጥንቃቄ ይዛ የምትጠቀምበት ደግሞ እንደ አጠቃቀሟ ለአመታት ሊቆይላት ይችላል፡፡
ይህን ፀጉር የሚጠቀሙ ሴቶች እድሜ እየገደባቸው እንዳልሆነ የምትናገረው ባለሞያ በአሰራዎቹ እድሜ ክልል ያሉ ትንንሽ ሴት ልጆች ሳየቀሩ በሂውማን ሄር መጠቀም መጀመራቸውን ነው የምታስረዳው። እንደ ባለሞያዋ አስተያየት ተሰሪዋ ወይም የሂውማን ሄር ተጠቃሚዋ የተለያዩ ፕሮግራሞች ሲኖሩና አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ቢጠቀሙ ምርጫዋ እንደ ሆነ ተናግራ የራስን ፀጉር ውበት እስከ ማሳጣት የሚደርስ ጉዳትና አንዳንዴም ሲወልቅ(ሲፈታ) የባዶነት ሰሜትን ፈጥሮ በራስ መተማመንን እንደሚጎዳ ተናግራለች።

zehabesha

No comments:

Post a Comment