ኖቬበር 4 2013 የምህረት አዋጁ መጠናቀቅ ተከትሎ በውጭ ሃገር ዜጎች ላይ የሚደረገው የቤት ለቤት አሰሳው አይቀሬነት እይተነገረ ነው ።
ለ 3 ወር የተራዘመው የሳውዲ አረቢያ መንግስት የስደተኞች ምህረት አዋጅ የፊታችን ሰኞ ኖቬበር 4 2013
መጠናቀቁን ተከትሎ ጭንቀት ስጋት እና ውጥረት በትለያዩ ሃገራት ዜጎች ላይ ነግሷል። ይህ አዋጅ ቀደም ብለው ከወጡት
የሳውዲ አረቢያ የስደተኞች ህግ የንጉሱ ትዕዛ ያረፈበት አሊያ « አምረል መሊክ » መሆኑ የተፈጻሚነቱ አይቀሬነት
በውጭ ሃገር ዚጎች ላይ ያለውን ስጋትን ከወትሯው ለየት እንዲል አድርጓታል ።
ከእንግዴህ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በፈለጉት የስራ ዘርፍ እንዳሻቸው ተሰማርተው መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ህጉ
እንደማይፈቅድላቸው ቀደም ብለው የተረዱ አያሌ የውጭ፡ሃገር ዜጎች ቤተስቦቻቸውን ወደ ሃገራቸው ሸኝተዋል አሊያም
ላይመለሱ ጎዛቸውን ጠቅልለው ከሃገሪቷ በመውጣት ላይ መሆናቸው እይተነገረ ነው።
በተለይ ያለመኖሪያ ፈቃድ ወልደው የከበዱ ኢትዮጵያውያን ሪያድ እና ጅዳ ላይ በብዛት እንዳሉ እይተነገረ ባለበት
በዚህ ቀውጢ ወቅት የነዚህ ዜጎቻችን እጣፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በህብረትሰባችን ውስጥ ያለው ጭንቀት ከመቸውም
ግዜ የከፋ አድርጎታል። ጅዳ እና ሪያድ ኢትዮጵያውያን በብዛት ይኖሩባቸዋል ተብለው የሚነገርላቸው አካባቢዎች
በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ፍተሻ እንደሚካሄድባቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች በመግለጽ ላይ ናቸው ።
ከጅዳው ይልቅ በብዛት በተለምዶ ባህር ሃይል እይተባሉ የሚነገርላቸው ድበር አቋርጠው ህገወጥ በሆነ መንገድ ወደ ሳውዲ ምድር የገቡ ዜጎቻችን ሪያድ ከተማ ውስጥ በተለምዶ መንፉሃ ኡም ሃማም ነስሪያ እና ነሲም የከተሙ በመሆናቸው በአካባቢው ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ ያለው ስጋት ጨምሯል። ትላንት ምሽት ሪያድ ከተማ መንፉሃ እና ነሲም አካባቢ አልፎ አልፎ ፍተሻ እንደነበር የሚጠቁሙ ምንጮቻችን ከግዜው ገደብ መጠናቀቅ ጋር ተዳምሮ ውጥረትን መፍጠሩ ይነገራል።
ከጅዳው ይልቅ በብዛት በተለምዶ ባህር ሃይል እይተባሉ የሚነገርላቸው ድበር አቋርጠው ህገወጥ በሆነ መንገድ ወደ ሳውዲ ምድር የገቡ ዜጎቻችን ሪያድ ከተማ ውስጥ በተለምዶ መንፉሃ ኡም ሃማም ነስሪያ እና ነሲም የከተሙ በመሆናቸው በአካባቢው ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ ያለው ስጋት ጨምሯል። ትላንት ምሽት ሪያድ ከተማ መንፉሃ እና ነሲም አካባቢ አልፎ አልፎ ፍተሻ እንደነበር የሚጠቁሙ ምንጮቻችን ከግዜው ገደብ መጠናቀቅ ጋር ተዳምሮ ውጥረትን መፍጠሩ ይነገራል።
በአብዛኛው ሪያድ ውስጥ በንግድ እና በት/ቤት አውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ስራ ላይ እንደተሰማራ
የሚነገርላቸው ዜጎቻችን የሳውዲ መንግስት ያወጣው ህግ ብዙም እንዳልተመቻቸው ይናገራሉ። በዚህም መስረት ከፊታችን
ኖቬበር 4 2013 የምህረት አዋጁ የግዜ ገድብ መጠናቀቁን ተከትሎ በእለት ተዕለተ እንቅስቃሴያቸው ላይ አሉታዊ
ተጸኖ ስለሚኖረው አብዛኛው የንግድ ቤቶች ተዘግቶ ሊውሉ እንደሚችል እና አብዛኛው የት/ቤት ትራንስፖርት አገልግሎት
የሚሰጡ የአውቶብስ ባለቤቶች የስራ ገበታቸው ላይ ሊገኑ እንደማይችሉ እየተነገረ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ በባህር
ወደ ሳውዲ አረቢያ ህገወጥ፡በሆነ መንገድ እንደገቡ የሚነገርላቸው ዚጎቻችን በየጎዳናው ያለ ስራ ለመባዘን ተገደዋል።
እንዚህ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው ዜጎቻችን ይልቅ ያለምንም ስጋት በነጻነት ሪያድ ከተማ ላይ በመንቀሳቀስ ላይ
መሆናቸው የነገራል።
በመጨረሻም የግዜ ገድቡ መጠናቀቁን ተከትሎ በሚደረገው አሰሳ ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያሉትን ወገኖች
እንደማይመለከት የሚናገሩ የሳውዲ ጸጥታ ሃይል ምንጮች የምህረት አዋጁን መራዘም አስመልክቶ እስካሁን ምንም ያሉት
ነገር እንደ ሌለ ለማረጋገጥ ተችሏል ።
ከዚህ በታች የሚታየው ሰዕላዊ መግለጫ በሪያድ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ የትላንት ውሎ ነው።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/11/04/34-6/
No comments:
Post a Comment