ኢሳት ዜና :- የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ደንብ ቁጥር 250/2003 ሽሮ እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀ ፤ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ለማቋቋሚያ
የወጣው አዋጅ ሀሙስ ይጸድቃል።በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች
ም/ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ የትራንሰፖርት እና የኢንዱስትሪ የቁጥጥር ስርዓቶች
ደህንነት ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉት የኢነርጂ፣ የባቡር ኔትዎርክ፣ የአቬሽን፣ የውሃ አቅርቦት ወዘተ የቁጥጥር
ስርዓቶች ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል መደንገጉን ይገልጻል።
የሳይበርና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ደህንነት የሳይበር እና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች የኢንተርኔት ራዲዮ፣ ኢንተርኔት ቲቪ፣ የቲቪና የሬዲዮ አገልግሎቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ዌብ ሳይቶች፣ ብሎጎች ወዘተ የሚያጠቃልል ሲሆን፤ ተደራሽነቱ ለሁሉም እኩል በመሆኑ
ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ካለው ፋይዳ በተቃራኒ ለጦርነት ቅስቀሳ፣ ለስም ማጥፋት ዘመቻ፣ የሃገርን ገጽታ ለማጉደፍ፣ ፀረ ልማት ፕሮፖጋንዳዎችን ለማሰራጨት፣ ፍርሃትንና አሉባልታን ለመንዛት፣ የኢኮኖሚ ስፔኩሌሽን ለማሰራጨት ወዘተ መጠቀሚያ ሊውሉ እንደሚችሉ ህጉ ይዘረዝራል።
ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገው ወታደራዊ የእዝና የቁጥጥር ስርዓት ደህንነት በመላ ሃገሪቱ ዳር ድንበር ላይ የመሸገው የሃገር የመከላከያ ኃይል እየዘመነ መሄዱ እና ኮምፒዩተርን መሰረት
ባደረገው የእዝና የቁጥጥር ስርዓት ላይ መመራቱ ተገቢ እና አዋጪ መሆኑ አያከራክርም የሚለው አዋጁ፣ በመሆኑም ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉት መሰረተ ልማቶች ደህንነት መጠበቅ ማለት ወታደራዊው የእዝ እና የቁጥጥር ስርዓቱ ደህንነት መጠበቅ ማለት ነው ብሎአል። ይሁንና ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ማንኛውም አደጋ በወታደራዊ የእዝ እና ቁጥጥር ስርዓቱ ላይ የሚደቀነው አደጋ መኖሩን የሚገልጸው አዋጅ፣ ይህ በብሄራዊ ደህንነት ላይ በቀጥታ የሚሰነዘር ጥቃት በአንድ በኩል ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ መሰረተ ልማቶች በመጠበቅ በሌላ በኩል ደግሞ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገው
ወታደራዊውን የእዝ እና ቁጥጥር ስርዓቱ በልዩ ሁኔታ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ያትታል። አዲሱ ህግ መንግስት ዜጎቹ በኢንተርኔት የሚያደርጉትን ማንኛውንም አይነት ግንኙነት ለመቆጣጠር የሚያስችለው ሲሆን፣ የቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤትን ብቃት ለማሳደግ ከፍተኛ ባጀት እንደሚመደብም ያትታል።
የሳይበርና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ደህንነት የሳይበር እና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች የኢንተርኔት ራዲዮ፣ ኢንተርኔት ቲቪ፣ የቲቪና የሬዲዮ አገልግሎቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ዌብ ሳይቶች፣ ብሎጎች ወዘተ የሚያጠቃልል ሲሆን፤ ተደራሽነቱ ለሁሉም እኩል በመሆኑ
ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ካለው ፋይዳ በተቃራኒ ለጦርነት ቅስቀሳ፣ ለስም ማጥፋት ዘመቻ፣ የሃገርን ገጽታ ለማጉደፍ፣ ፀረ ልማት ፕሮፖጋንዳዎችን ለማሰራጨት፣ ፍርሃትንና አሉባልታን ለመንዛት፣ የኢኮኖሚ ስፔኩሌሽን ለማሰራጨት ወዘተ መጠቀሚያ ሊውሉ እንደሚችሉ ህጉ ይዘረዝራል።
ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገው ወታደራዊ የእዝና የቁጥጥር ስርዓት ደህንነት በመላ ሃገሪቱ ዳር ድንበር ላይ የመሸገው የሃገር የመከላከያ ኃይል እየዘመነ መሄዱ እና ኮምፒዩተርን መሰረት
ባደረገው የእዝና የቁጥጥር ስርዓት ላይ መመራቱ ተገቢ እና አዋጪ መሆኑ አያከራክርም የሚለው አዋጁ፣ በመሆኑም ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉት መሰረተ ልማቶች ደህንነት መጠበቅ ማለት ወታደራዊው የእዝ እና የቁጥጥር ስርዓቱ ደህንነት መጠበቅ ማለት ነው ብሎአል። ይሁንና ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ማንኛውም አደጋ በወታደራዊ የእዝ እና ቁጥጥር ስርዓቱ ላይ የሚደቀነው አደጋ መኖሩን የሚገልጸው አዋጅ፣ ይህ በብሄራዊ ደህንነት ላይ በቀጥታ የሚሰነዘር ጥቃት በአንድ በኩል ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ መሰረተ ልማቶች በመጠበቅ በሌላ በኩል ደግሞ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረገው
ወታደራዊውን የእዝ እና ቁጥጥር ስርዓቱ በልዩ ሁኔታ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ያትታል። አዲሱ ህግ መንግስት ዜጎቹ በኢንተርኔት የሚያደርጉትን ማንኛውንም አይነት ግንኙነት ለመቆጣጠር የሚያስችለው ሲሆን፣ የቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤትን ብቃት ለማሳደግ ከፍተኛ ባጀት እንደሚመደብም ያትታል።
መከላከያ ኦዲት እንዳይደረግ የሚያስችል አዋጅ ተረቀቀ
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ
እንደዘገበው በ2004 በጀት ዓመት ባልተሟላ ሰነድ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ባላይ ወጪ በማድረጉ በፌዴራል ዋና
ኦዲተር መ/ቤት ጠንካራ ትችት የቀረበበት የመከላከያ ሚኒስቴር የሒሳብ መዛግብቱን ዋናው ኦዲተርን ጨምሮ ለማንኛውም
አካል ሚስጢር ማድረግ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል።
አዲሱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ሰነድ በአንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት አገራዊ ጥቅምንና
ደህንነትን ለመከላከል ሲባል እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና
ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለጹ የማድረግ ስልጣን ተሰጥቶታል።
በአንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት ሚኒስቴሩ ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባቸው ለአገር መከላከል
ዓላማ የሚውሉ ዕቃዎችና መሳሪያዎች ከጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በነጻ እንደሚያስገባ ተፈቅዶለታል። ዕቃዎቹን
እንዲያስፈትሽ ወይም ሰነዶቹን እንዲያስመረምር እንደማይገደድም ተደንግጓል።
የመከላከያ ተቋማት በሠላም ጊዜ የሚኖራቸውን የማምረትና አገልግሎት የመስጠት አቅም ለገቢ ማስገኛ ተግባር
እንዲውል በማድረግ የሚገኘውን ገቢ፣ ለመከላከያ ጠቀሜታ የማያስፈልጉ ንብረቶችን በማስወገድ የሚገኘው ገቢ፣
በተቆጣጣሪ ባለስልጣንነት ከሚመራቸው ድርጅቶች የሚገኘውን የትርፍ ድርሻ እና ከሠላም ማስከበር ስምሪቶች የሚገኘው
ገቢ በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ እንዲመረመር እንደሚያደርግ በረቂቅ አዋጁ
መደንገጉን ጋዜጣው ዘግቧል።
የፌዴራል ዋናው ኦዲተር ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ማጠናቀቂያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የ2004
ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት መሰረት የመከላከያ ሚኒስቴር ባልተሟላ ሰነድ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ካደረጉ ዘጠኝ ያህል
የመንግስት ተቋማት መካከል 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በማስመዝገብ የላቀ ድርሻ መያዙ ይፋ ከተደረገ በኋላ
የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ጨምሮ ሌሎች የመከላከያ ሹማምንት ሪፖርቱን ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ጋዜጣው
አስታውሷል።
በህወሀት ታጋዮች ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሚኒስቴር ወጪውን በጄኔራል ኦዲተር እንዳይመረመር ለማስደረግ
መቻሉ፣ በሚኒስቴሩ ውስጥ የሚታየውን ገደብ የለሽ የገንዘብ ዘረፋ እንደሚያባብሰው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ጸረ
ሙስና ኮሚሽንም ደፍሮ መከላከያን እስካሁን ለመመርመር አልቻለም። አብዛኛዎቹ የህወሀት ጄኔራሎች በመከላከያ ስም
ከቀረጽ ነጻ በሚያስገቡዋቸው እቃዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በሀብት ጣራ ላይ እንዲቀመጡ እንዳደረጋቸው ኢሳት መዘገቡ
ይታወቃል።
ቁጫ ዛሬ በተቃውሞ ሰልፍ ስትናወጥ ዋለች
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ አንዴ ሲሞቅ ሌላ ጊዜ ሲቀዘቅዝ የነበረው የቁጫ ተቃውሞ በዛሬው እለት በሰላም በር ከተማ ተጠናክሮ መካሄዱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
ዛሬ ተቃውሞውን ያካሄዱት ተማሪዎች ሲሆኑ ፣ ተማሪዎችም ላቀረብነው ጥያቄ መልስ የማይሰጠን ከሆነ ትምህርት አንማርም ብለዋል።
ተቃውሞውን አስተባብረዋል የተባሉ መምህራንም በአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተው ተቃውሞን የመሩትን እንዲያጋልጡ
ተጠይቀዋል። ልዩ ሀይል ከተማዋን ተቆጣጥሮ በተማሪዎች ላይ ድብደባ የፈጸመ ሲሆን 15 የሚሆኑ ወጣቶችም ተይዘው
ታስረዋል። ተማሪዎቹ በቋንቋችን እንማር የሚሉ ጥያቄዎችን ሲያሰሙ ውለዋል።
ከዚህ ቀደም ከ60 ያላነሱ ሰዎች ታስረው መፈታታቸው ይታወቃል። 40 የሚሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ደግሞ ከስራ
እንዲባረሩ ተደርጓል። እንዲሁም የወረዳው ነዋሪዎች መረጃዎችን ለመለዋወጥ ይጠቀሙባቸዋል ያላቸውን 160 ባጃጅ
እየተባሉ የሚጠሩ ተሽከርካሪዎችን አስሯል።
በወረዳው ውስጥ ባሉ 26 ቀበሌዎች ያለው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመሩም ታውቋል።
መንግስት አገሪቱ በሽብር ጥቃት ኢላማ ውስጥ ገብታለች አለ
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ
ሽብር ግብረሀይል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላላፈው መልእክት አልሸባብና በኤርትራ የሚደገፉ ሀይሎች በመላው
አገሪቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል ብሎአል። ዜጎች እራሳቸውን ለመከላከል
አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልጿል።
ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፍተሻዎች ሲደረጉ የሰነበቱ ሲሆን፣ የትናንቱ ማስጠንቀቂያም ይህን ተከትሎ
የተሰጠ ነው። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ የሽብር ሀይሎች ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጅተዋል ቢልም እነዚህን ሀይሎች
ከመዘርዝር ተቆጥቧል። መንግስት በኤርትራ የሚደፉ ሀይሎች ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው
አላሳወቀም። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ አሸባሪዎች በማለት የፈረጃቸው ድርጅቶች ግንቦት7፣ ኦነግና ኦብነግ
ናቸው። መግለጫውን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ኬላዎች ላይ ፍተሻ በመካሄድ ላይ
ነው። መንግስት የሽብር ጥቃት አደጋ ተደቅኖብኛል ቢልም ከኢትዮጵያውያን በኩል የሚቀርበው ምላሽ ተቃራኒውን እየሆነ
ነው። በማህበራዊ ድረገጾች የሚወጡ እንዲሁም ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች ፣ ” መንግስት ራሱ ፈርቶ ህዝቡን
እያስፈራራ መሆኑን” የሚያመለክቱ ናቸው። ብዙ አስተያየት ሰጪዎች የመንግስትን ማስጠንቀቂያ አይቀበሉትም። አንዳንዶች
ዜጎች ራሳቸውን ከመንግስት የተቀነባባረ የሽብር ጥቃት መጠበቅ እንዳለባቸው ይመክራሉ።የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት
ትናንት ለፓርላማ ባቀረበው ሪፖርት የ2006 ዋነኛ አጀንዳው ኢትዮጵያን ከሽብር ጥቃት መከላከል መሆኑን አሳውቋል።
ኢትዩጵያ በምግብ እጥረት የተነሳ ከልጆቹዋ በየዓመቱ 144 ቢሊዮን ብር ታጣለች ተባለ
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወጣት
እስከ አዋቂ ያለው ከግማሽ በላይ የሚሆነው ኢትዮጵያ በልጅነቱ በቂ ምግብ ሳያገኝ ተጎድቶ እንደሚያድግ
የተመለከተው በኢትዮጵያ ይፋ በሆነው the cost of hunger in Ethiopia ጥናት ውስጥ ነው።
67 ከመቶ የሚሆነውና ከ15 አስከ 64 የእድሜ ክልል ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊ ጠንካራ ሰራተኛ ቢመስልም በልጅነቱ ያጣው የተመጣጠነ ምግብ አቀንጭሮትና አቀጭጮት አቅም አሳጥቶት በስራው ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል።
እነዚህ ሰዎች በልጅነታቸው የተፈለገውን ምግብ አግኝተው ቢሆን ኖሮ በያመቱ 53.6 ቢሊዎን ብር ማዳን ይችሉ ነበር ተብሏል።
ልጆቹ ሲያድጉ አንድም በጤና ምክንያት ከስራ ይቀራሉ ሌላም ለህክምና ገንዘብ ያወጣሉ። በዚህም ምክንያት 4.8 ቢሊዎን የስራ ስዓት ሲያባክኑ፣ አገሪቱ 40 ቢሊዎን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ታጣለች።
በትምህርት በኩልም ቢሆን አእምሮአቸው ብዙም ያልዳበረ በመሆኑ የተመጣጠነ ምግብ አግኝተው ካደጉት አገሮች በበለጠ ትምህርታቸውን ይደግማሉ።
በ2001 የትምህርት ዘመን ብቻ በዚሁ ችግር ውስጥ ያለፉ ከ152 ሺህ በላይ ታዳጊዎች ወደ ቀጣይ ክፍል
ሳያልፉ ቀርተዋል። ትምህርት መከታተል ተስኗቸው ያቋረጡም ብዙ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ተምረው ቢሆን ኖሮ
እውቀታቸውን አዳብረው በያመቱ ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው 625 ሚሊዎን ብር ተጨማሪ ገቢ ያስገኙ ነበር ይላል the
cost of hunger in Ethiopia ጥናት ። ጥናት በኡጋንዳ ግብፅና ሲዋዚላንድ ተመሳሳይ ምርምር አድርጎ
የኢትዮጵያ ችግር የከፋው መሆኑን ገልጿል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2006 አስከ 2015 ኢትዮጵያ ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ 144 ቢልየን ብር
ታጣለች ፡፡ ችግሩ ቀጣይ ና አሳሳቢ ነው የሚሉት ባለሙያዎች ፣ የምግብ እጥረት የቀጣዩ ትውልድ ፈተናዎች ይሆናሉ
ይላሉ፡፡
በመላ ሀገሪቱ ከ5 ሚልዮን በላይ ዜጎች ነገ ሰለሚበሉት ዋስትና እንደሌላቸው የፌድራል አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሺን መረጃ ያሣያል፡፡
ESAT
No comments:
Post a Comment