Thursday, November 7, 2013

ዋልያ በ2ተኛ ቡድኑ ወደ ኬንያ ያመራል!!ፕሪሚየር ሊጉ—ቆመህ ጠብቀኝ???

ከ20 ቀናት በኋላ ሴካፋ በኬንያ ይጀመራል፤11 ንድ አባል ሀገራት እና 3ተጋባዞች በዉድድሩ ይጠበቃሉ፤ማላዊ፤ኮትዲቫር እና ዛምቢያ በቻን ቡድናቸዉ ልምድ ይወስዳሉ፤ዋልያዉም በጥር ወር የቻን ዉድድር ይጠብቀዋል፤ዛሬ ዋና አሰልጣኙ ሰዉነት ቢሻዉ እንደተናገሩት በ2ተኛ ቡድናቸዉ ወደ ኬንያ እንደሚያመሩ አሳዉቀዋል፤
ይህ ማለት አሁን በተደጋጋሚ በማጣሪያ ጨዋታና በአፍሪካ ዋንጫ የተሰለፉ ተጫዋቾች እረፍት ያገኙና እድል ያልተሰጣቸዉ ተጫዋቾች በኬንያ ይጫወታሉ፤በተለይም በተጠባባቂ ወንበር ላይ ያሉ ተጫዋቾች ከ23ቱ ዉጪ የነበሩ እና እራሳቸዉን ለማሳየት በዉድድሩ ይሳተፋሉ፤
36ተኛዉ የሴካፋ ዉድድር ኡጋንዳ ላይ ሲዘጋጅ ምክትል አሰልጣኙ ስዩም ከበደ ነበር ቡድኑን ይዞ የሄደዉ..በጥቂት ጨዋታዎች ላይ ዋናዉ አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ተገኝተዋል፤በኬንያዉ ሴካፋ ማን ቡድኑን ይዞ እንደሚጓዝ አልታወቀም፤
በነገራችን ላይ የአሁኑ ዋልያ ከሱማሌ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በኋላ የዉድድር ጨዋታ ያደረገዉ በታንዛኒያ ዳሪሰላም ነበር፤ከኬንያ ማላዊ እና ሱዳን ጋር ነበር የተደለደለዉ —ከማላዊና ሱዳን ጋር 1 አቻ ወጥቶ በዝናብ ጨዋታ በኬንያ 2ለ0 ተሸንፎ ነበር ከምድቡ የቀረዉ..ከዛ መልስ ግን ለአፍሪካ ዋንጫ ሱዳንን አሸንፎ ማለፍ ችሏል፤
የኬንያዉ ሴካፋ የምድብ ድልድል ይፋ አልሆነም፤ባለፈዉ አመት በ2ተኛ ቡድኑ ከምድቡ 3ተኛ ሁኖ ማለፍ ቢችልም በኡጋንዳ ተሸንፎ ወድቅዋል፤ዘንድሮስ???የሴካፋ ዋንጫ ወደ አዲስ አበባ ካመጡት አሰልጣኞች መሀል ሰዉነት የተሻለ ሪከርድ አላቸዉ፤አንዴ በምክትልነት ከዛም በዋና አሰልጣኝነት ከዉጪ ዋንጫ አምጥትዋል፤
ኢትዮጲያም በአጠቃላይ እስካሁን 5ት ጊዜ ዋንጫ አግኝታለች፤አንዳንድ ጊዜ 4ት ጊዜ ስለማግኘትዋ ይነገራል፤በ1957 ኢትዮጲያ አዲሱን የምስራቅና አፍሪካ ዋንጫ ስታዘጋጅ ዋንጫ አንስታለች፤የ1980ዉን የነዳኙ ገላግሌን ደግሞ እናንተ መስክራችሁዋል(ባሼ ከሆናችሁ)..የሰዉነትን 2ት ዋንጫ ደምሩበት!!የአዲስ አበባዉን የአላሙዲ ሲንየር ቻሌንጅ ካፕ ስታክሉበት 5ት አልሆኑም??
ለማንኛዉም ከካላባር መልስ ልብ አንጠልጣዩ የዋልያ ጉዞ በኬንያ ይቀጥላል፤አሁን ጥያቄ የሚሆነዉ ፕሪሚየር ሊጉ እንዴት እንደሚቀጥል ነዉ፤እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ደደቢት ብዙ ተጫዋች ስላስመረጡ ጨዋታ አልፍዋቸዋል፤አሁን ደግሞ ሌሎቹ ሲያስመርጡ ያርፋሉ..ፕሪሚየር ሊጉ ቆመህ ጠብቀኝ ሊሆን ነዉ ማለት ነዉ፤2ተኛዉ ቡድን ከሴካፍ ሲመለስ የቻን ዉድድር በደቡብ አፍሪካ ይካሄዳል፤እንደገና ዋናዎቹ ሲጠሩ ሊጉ ክፉኛ የጨዋታ መዛባት ያጠቃዋል፤በዚህ ብቻ ቢያበቃ መልካም ነበር…የ30ኛዉ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያም ወዲያዉ ብቅ ይላል፤እናም ኢ.እ.ፌ መፍትሄ ሊያበጅለት ይገባል!!!

 http://www.ethiotube.net/

No comments:

Post a Comment