ቀን ጥቅምት 27/2006ዓ.ም
የተከለከለውን እንደተፈቀደ...
ከኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል
እኛ ኢትዮጵያውያን በቀደመው የረጅም ዘመን ታሪካችን አያሌ የታሪክ ትሩፋት የነበረን ሕዝቦች
ነበርን። ዛሬ ላይ ሆነን ይህን ኃላፊነት የጎደለውን አስተዳደር ስናጤን፤ የእኛነታችን መገለጫ የሆኑ
እሴቶቻችን ሁሉ ተነጥቀን፣ ታሪክ አልባ፣ እምነት አልባ፣ ዜግነት አልባ ሆነን፤ በአገር ቤትም ሆነ ባስደት
የምንንከራተት ወገኖች የመከራ ቁናችንን መስፈር ከጀመርን ሃያ ሶስት ዓመታትን አስቆጥረናል።
በእነዚህ የመከራና የመካካድ ዘመናት ውስጥ በአንድነት የኖርን ሕዝብ መሆናችን ቀርቶ በጐሳ
ፖለቲካ ሊያናቁሩን ሞክረዋል። የሀገራችንን የባህር በር በፈቃዳቸው ለጐረቤት ሀገር ሸልመዋል። እንደ
ግል ንብረታቸው ከብሔራዊ ድንበራችን ቀንሰው ለሱዳን ገፀ-በረከት አበርክተዋል። የመናገርና ሐሳብን
በነፃነት የመግለፅ ሕገ-መንግስታዊ መብታችንን እንዳንጠቀምበት ለጉመውናል። ለፍትህ ለዲሞክራሲና
ለሰላም የታገሉ ሀቀኛ የሀገሪቱ ልጆች በግፍ ተገለዋል። አካለ ጐደሎ ሆነዋል። በሺህ የሚቆጠሩ ወደ ወህኒ
ቤት ተወርውረዋል። በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ተሰደዋል። እህቶቻችን ለአረብ ሀገራት እንደ ሸቀጥ
ተሸጠዋል። በአጠቃላይ በቃላት የማይገለፅ ሁለ ገብ ብሔራዊ ውርደት እኛም ሀገራችንም ተዋርደናል።
ይህን ሁሉ በደል መቋቋም ተስኖን የሀገሪቱን ብሔራዊ ድንበር ጥሰንም ይሁን በሕጋዊ መንገድ
በመውጣት ስደትን እንደ እድሜ ማራዘሚያ ሰንቀን ስንኮበልል ባህር የሚያሰምጠን፣ የውስጥ የሰውነት
አካላችንን እንደ ኪስ ቦርሳ የምንዘረፍ፣ እንደቁሳቁስ በኮንቴነር ታሽገን ዘግናኝ የሞት ፅዋ የምንጨልጥ፣
በአጠቃላይ በዚህች ምድር ላይ ያለ የመከራ ዓይነት ሁሉ ተሸከሙ የተባልን ይመስል፣ በነዚህ ስለ
ሰብአዊነት ለማሰብ በጨለመባቸውና የአውሬ ባህሪ በተጠናወታቸው ግፈኞች ያለ ቀባሪ እንድንቀር
የተደረግንና በእነሱ የግፍ አለንጋ እየተገረፍን በነሱ ፈቃድ ሳይሆን በፈጣሪ ቸርነት ከዚህች ዕለት ላይ
ከነመከራችን ደርሰን እንገኛለን።
ይህን ሁሉ ሰብአዊ ክብራችንን ያሳጣን ዘረኛ አስተዳደር፤ ይህ አልበቃ ብሎት በታሪካችን፣
በሐይማኖታችን፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጋችን ሳይቀር የተከለከለን ድርጊት የመንግስት የፀጥታና የደህንነት
አስከባሪ ነን በሚሉ አስተሳሰበ ድውያን ሰሞኑን በአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የብሔራዊ ምክር ቤት
2
አባል በአቶ አበበ አካሉ ላይ አስገድደው የአልኮል መጠጥ በመጋት የተፈፀመባቸውን የወሲብ ጥቃት
ወንጀል ማህበራችን በፅኑ ያወግዛል። በረጅም ዘመን የነጻነት ታሪካችን በግብረ ሰዶማዊነት ራሳቸው
ፈቅደው ከተሰማሩ ሰዎች ውጭ ሕግ እናስከብራለን በሚሉ ኃይሎች እንዲህ አይነቱ ነውር በእኛ ትውልድ
ሲፈፀም በማየታችን በህሊናችን ውስጥ ጊዜ የማይሽረው ጠባሳ አሳርፈውብናል። የመጨረሻውንም
የውርደት ሸማ ሊያከናንቡን በቅተዋል።
ስለሆነም የየትኛውም የሐይማኖት ተቋም መሪዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ተቋማት
መሪዎችና አባላት፣ ከማንም በላይ የመከራው አለት የተጫነባችሁ ውድ የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤ እነዚህ እንደ
ማፊያ ቡድን ከየቦታው ተጠራርተው የመጡብንን የጥፋት መልዕክተኞች ሊበድሉን፣ ሊያዋርዱን፣
ሊበቀሉን በበረሃ አቅደው ከመጡት በላይ ለመፈፀም በቅተዋልና፤ በጋራ በቃ ልንላቸው ይገባል። ከዚህ
የከፋ የቁም ሞት የለም። አንዴ ተፈጥረን ሁለቴ መሞት ሊበቃን ይገባል። የግፍ ፅዋ በሀገራችንና በእኛ ላይ
ሞልቶ ፈሷልና ለቀጣዩ ትውልድ የምናስረክበው አገርና ታሪክ ተሟጦ ሳይጠፋ፤ ሁላችንም ከዚህ ጐጠኛ
ስርዓት ሀገራችንንና እራሳችንን ነፃ ለማውጣት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ታሪክ ለመስራት በጋራ እንነሳ
ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርክ!
ኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል
zehabesha
No comments:
Post a Comment