Wednesday, November 6, 2013

ኢህአዲግና ስርዓት አልባው ማኪያቪሊ

የማኪያቪሊ ፖለቲካዊ ፍልስፍናና የኢሀዲግ አገዛዝ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ አንድ የሚያደርጋቸው ነገሮች አያሌ ነው የማኪያቪል ፍልስፍና ለገዚዎች እንጂ ለህዝቡ ደንታ የማይሰጠው ሲሆን ገዢዎች ስልጣን ላይ መቀመጥ ከፈለጉ ስልጣናቸውን ያለምን ተቀናቃኝ ይዘው እንዲጓዙ ማድረግ የሚገባቸውን ነገሮች ይተነትናል ይሄ በመርዝ የተሸፈነ የማኪያቬሊ የፖለቲካ ፍልስፍና አያሌ የአለማችን ገዢ ዎች ሲያራምዱትና ለመንግስታቸው ምረኩዝ አድርገው ሲዘልቁበት በስፋት ይስተዋላል ከእነዚህም አንደኛው ኢህአዲግ ነው
ስለፖለቲካና ስለገዢ ስናነሳ ከሰላማዊ ፖለቲካ አስተምህሮ ውጪ ሆኖ የምናገኘው ማኪያቪሊ በ1469 ዓ.ም በጣሊያኗ ፍሎረንስ ከተማ የተወለደው መኪያቪሊ በወቅቱ ወጣት ሳለ ቀድሞ የነበረው የንጉሳዊያን አስተዳደር በለውጥ ስለተገረሰሰ በምትኩ በከተመዋ የሪፐብሊክ መንግስት በመመስረቱ 29ዓመት ይሞላው የነበረው ኒኮሎ ማኪያቪሊ በአዲሱ መንግስት ኃላፊነትን ተጎናጽፏላ ፡፡ ነግር ግን ብዙም ሳይቆይ በ 1512 ዓ ም የፍሎረንስ ሪፐብሊክ በፈረንሳይና በሮማው ጳጳስ የዳግማዊ ጁሊየስ ኃይሎች ባደረጉት ፍልሚያ ጳጳሱ ስላሻነፉ ቀድሞ የነበረውን የንጉሳዊ የሚዲቼን ቤተሰብ ወደ ዳግም ስልጣን አመጡት፡፡
ኪዚህ በኋላ ነው እንግዲ ማኪያቪሊ ለመንግስታት ወይም ለገዢዎች መከተል የሚገባቸውን መርዝ ምክሩን በመጸሀፉ መከተብ የጀመረው ፡፡ ፖለቲካዊ ስልጣን መያዝ ወይም አስጠብቀህ መያዝ ከፈለግህ በማለት መርዙን ይተፋል ፖለቲከኛን ስልጣን ለምን ትፈልጋለህ ተብሎ መጠየቅ አይገባውም የሚለው ማኪያቪሊን ልክ ሀኪም ፊት የቀረበን በሽተኛ መዳን ትፈልጋለህ የማለትን ያክል አይረቢ ጥያቂነው ይለናል ፖለቲከኛው ስልጣኑን ሲይዝ እርሱ የሚፈልገውን ነገር ያድርግ እንደማለት ነው ብለን ልንፈታው እንችላለን በእርሱ ጸሁፍ ውስጥ ግን ፖለቲከኛው ስልጣን ሲይዝ እንደዚህ አይነቶችን ነገሮች እንዲጠቀም ይመክረዋል፡፡
1. ነጻነትን መስጠት ሳይሆን ጭቆናን ማስወገድ
አንድ ዜጋ በህዝብ ተቀባይነት አግኝቶ ገዢ ከሆነ የህዝቡን ወዳጅነት ለመጠበቅ ማድረግ የሚገባው ቀላል መንገድ አለ ይህ ደግሞ ከህዝቡ የሚቀርብለት ነገር ደግሞ ከህዝቡ የሚቀርብለት ጥያቄ አትጨቁነን የሚል ነው ሚኪያቪሊ መንግስት እንደመንግስትነቱ የብዙሀኑን ህዝብ ምኞት ሊያዳምጥ ይገባል ብዙሀኑ ደግሞ የሚፈልገው በደህንነቱ መኖር ነው ድንጋጤና ኮሽታ ለተራው ህዝብ አስፈላጊ አይደለም ስለዚህ የተራው ህዝብ ጥያቄ አንድና አንድ ከጭቆና መራቅ ነው በዚህ ሁኔታ አንድ መንግስት ስልጣኑን ከያዘ በኋላ ለማደላደል ከፈለገ የተራውን ህዝብ ወዳጅነት መጠበቅ አለበት በእርግጥ ይለናል‹‹ገዢው አካል የሰዎችን ንብረት ወይም ክብር ላይ ጥቃት እስካልሰነዘረ ድረስ ህይወታቸውን በእርጋታ ያለአንዳች ማጉረምረም ስለሚመሩ ጥቂት ነፃነት ፈላጊዎችን ብቻ ማጋፈጥ ይቻላል እነዚህን ደግሞ ለመቆጣጠር እጅግ በርካታ መንገዶች አሉ ›› ይህንን ቃል በግልጽ ስንፈታው ነአፈንጋጮች ላይ አልባሌ የሆነ ክስና ፕሮፖጋንዳ መንዛት እንደ አስፈላጊነቱ ማሰር ወደሚለው ድምዳሚ ያመራናል፡፡
ይህንን አይነቱን የፖለቲካ አስተምህሮ ገዢ ከስልጣኑ እንዳይወርድ ስልጣኑም እድሜ ይፍታህ እንዲሆን የሚጠቀሙበት መንገድ ነው ሌላኛው መርዕ
2. የብዙሀኑን የመጀመሪያ ፍላጎት ሟሟላት
ብዙሃ ስንል ከመላው ሀገር ህዝብ መሃከል የሚበዙተ ተራ ተርታ ህዝቦች ናቸው እነዚህ ሰዎች ደግሞ በሚታይ አብረቅራቂ ምስልና ንግግር ልቦቻቸውን መግዛት ይችላሉ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚነገራቸው ተረትና ትረካዎች በሚያዩት መግነጢሳዊ ምስል ተረስተው መኖር የሚችሉ ናቸው፡፡
ስለዚህ በብኃኑ የሚታየውን ፍላጎት ሟሟላት ከቻለ እነዚህን ህዝቦች አመጽ ሳያምጹ ይዞ መሄድ እጅግ በጣም ቀላል ነው ምክንያቱም ከላይ እንዳየነው ተርታው ህዝብ የእለት ጉርሻውን ለማግኘት ደፋ ቀና የሚልና ከዙህ ነገር አልፎ አመጽ ሊያስነሳበት የሚችል አቅም አይኖረውም ዋናው ነገር ኮሽ ሳይል ኮሽ ሳይል ስራውን እንዲሰራና የእለት ጉርሱን እንዲያገኝ የሚያስችለውን ደህንነት መዘርጋት ነው፡፡
እንደዚህ አይነት አሰራሮች በፖለቲካው መስክ ገዢው ፓርቲ አብዝቶ የሚጠቀምባቸው አልፎም ቅቤ ምላሱ በሆነ አነጋገር ህዝቡን/የተርታውን/ የልብ ትርታ የሚያገኘበት /የሚቆጣጠርበት/ ዘዴ እሆነ አሁን ባለነው ዘመንም ገዚዎቻችን በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ እተጠቀመበት ይገኛል ለህዝቡ የሚያቀርባቸውን መረጃም እጅግ በጣም በጥቂቱ እውነታን የተላበሱ አልያም ተጠንቶበትና ቂቤ ተቀብቶ ተውኔት በሆነ ምልኩ አስፈሪና ልብ አንጠልጣይ መረጃዎችን በተደጋጋሚ ለዚህ ተርታው ህዝብ ገጸበረከት አድርጎ ያቀርብላቸዋል፡፡
3. ሊላኛው የማኪያቬሊ አስተምህሮ ‹‹ ሰዎች ከሚወዱት ይልቅ የሚፈሩትን ሰው ማስቀየም ይፈራሉ›› ይለናል
መንግስት ወይም ገዢ ከሚወደድ ይልቅ ቢፈራ መልካም ነው መወደድ ከሚያመጣው ክብር ይልቅ መፈራት እጥፉን ያመጣል የሚለው ማኪያቬሊ ፍርሃት ውስጥ ያሉት ሰዎች መቼም ሊሰብሩት የማይቻላቸውን ደፍረው ለመስበር ቢያስቡ እንኳ ሊያገኛቸው በሚችለው መከረና እንግልት የሚጠበቅ ስልጣን መገንባት ይችላል፡፡ ነገር ግን ይለናል ለመፈራት ተብሎ ብቻ በህዝብ ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑትን ፍርሃት ማንገስም ተገቢ አይደለም እነዚህ ሁሉ ፍርሃቶች የተጠኑና አስፈላጊነታቸው የታመነ መሆን አለበት ሁል ጊዜም ቢሆን በህዝቡ ውስጥ ያለው የገዢ ፓርቲ ጥቅም ተጋሪዎችና ጫንቃቸውን የሚያደልቡ እንደማይጠፉ ሁሉ ምንም አይነት ጥቅምን የማያገኙ እና ሌሎች ነጻነታቸውን የሚገፈፉ በርከት ያሉ ናቸው ታዲያ መንግስት ከእነኚህ ጥቅም ከጎደለባቸው ክፍሎች ዓይኑን መንቀል የለበትም ምክንያቱም እነዚህኛዎቹ ከበዙ አመጽንና ለመንግስቱ እድሜ ማነስ የላቀ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ናቸው ከእነዚህ መካከል እጅግ በጣም ጽንፈኛ ተቃዋሚዎች ሊያጋጥሙ ይችላል ስለዚህ እነዚኽን ጽንፈኛ ተቃዋሚ ዎች ይዞ መንግስቱን በተረጋጋ ሁኔታ ማቆም አይችልምና አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡ ይህም ጽንፈኛ ተቃዋሚዎችን መግደል፡፡
ፖለቲካ እንደ ሀይማኖት ሁሉ የራሱ የሆነ ህግ አለው ሀይማኖት በአንተ ላይ ሊደረግብህ የማትወደውን ነገር በሌላ ላይ አታድርግ ሲል ይመክረናል፡፡ ፖለቲካ ደግሞ በአንድ ሰው ላይ መጥፎ ነገር ማድረግ የምትፈልግ ከሆነ ፊትለፊት አትጋፈጥ በእጅ አዙር ወንጀለኛ አድረገው አሊያም ሊላ ነገር እንዲህ አይነቶችን ነገሮች በተደጋጋሚ ማየት የተለመደ ነው በፖለቲካ አለመስማማት ሲመጣ ሙሰኛ ፣አክራሪ፣ተሳዳቢ ወዘተርፈ እተባለ በእጅ አዙር የተቸነከሩትን ህሊና ይቁጠረው ለነገሩ ህሊናም ከዋለበት ነው የሚዳኘው
‹‹ መሪ ከእርሱ ፍላጎት ውጪ በተጻረረ መልኩ የቆመ ከሆነ እምነት ሊኖረው አይገባውም ነገር ግን ሩህሩህ፣ታማኝ፣ሀቀኛ፣ሐይማኖተኛ መምሰል ጥሩ ነው በተለይም ህዝብ ውስጥ ተሀወተሩትን በህሎች ላለማስደፈር የሚተጋ መምሰል አለበት፡፡ እያለ የሚተነትነው ማኪያቪሊ በነገሮች ማስመሰልንና ብሎም ውስጥ ድረስ ገብቶ ሐይማኖታችን የእርሱ አቀንቃኝ እንዲሆኑ ማድረግ ነው


 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/11/05/45565/

No comments:

Post a Comment