Friday, November 1, 2013

ሳያድግ አርጅቶ ሲወለድ ለሞተው ሙሾ




አእምሮው ጠልሽቶ እርግማን አዝምሮ፣
በተንኮል በክፋት ልቦናው ታውሮ፣
ክቡር ሕሊናውን ለጥቅም ለውጦ፣
የነወረ ሐሳቡን በወርቅ ለብጦ፣
ቅንጣት ታህል እንኳን ቅንነትን አጥቶ፣
ሲወለድ መሞቱ ጭራሽ ተዘንግቶ፣
ዓመታት አባክኖ የሚቀብረው ጠፍቶ፣
እንደሌላው ሲሞት ሳያድግ አርጅቶ፣
ይቀበር ይባላል ወግ አይቀርም ከቶ፡፡
ይሄም ኖርኩ ይላል ድንቄም ኑሮ መኖር፣
ገና ድሮ ሞቶ ሳይቀበር ቢቀር፡፡
ዋዬ ወየው!!!!!!!

የታላቋ ቀን ልጅ 1994 ዓ.ም (Son of the great day 2002)

No comments:

Post a Comment