Friday, November 8, 2013

የጌታነህ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ


ከዳዊት በጋሻው
2013 Orange African Cup of Nations: Zambia v Ethiopiaየዋሊያዎቹ ዘጠኝ ቁጥር ጌታነህ ከበደ ከደቡብ ክልል ከተገኙት እንደእነ አዳነ ግርማ፣ደጉ ደበበና ከመሳሰሉት ዕንቁ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጌዲዮ ዞን የተወለደው ጌታነህ ባለፉት ዓመታት በኢት ዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጎልተው ከወጡትና ዓመቱን በስኬት ካጠናቀቁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።
ጌታነህ ከበደ ከደደቢት ክለብ ጋር የ2005 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያሸነፈ ሲሆን፤ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋችና ኮከብ ግብ አግቢም በመሆን ተመርጧል።
ታዲያ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ብሔ ራዊ እግር ኳስ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ መሳተፉን እንዲሁም በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ያሳየውን ውጤት ተከትሎ ጌታነህ የበርካታ ክለቦች ዓይን ማረፊያ ለመሆን ችሏል። በመሆኑም የደቡብ አፍሪካውን ቢድቬስት ዊትስ ዩኒቨርሲቲ ቡድንን ተቀላቅሏል።
ወደ ደቡብ አፍሪካ ካቀና በኋላም በደደ ቢትና በብሔራዊ ቡድኑ የነበረውን ብቃት በቢድቬስትም መድገም ችሏል። ለአብነትም ስምንት ቡድኖች ብቻ በሚሳተፉበት የኤምቲኤን ጨዋታ ላይ ተሰልፎ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሁለተኛው ኮከብ ተጫዋች መሆን የቻለ ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግም ለቡድኑ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ይህ የሚያሳየው ታዲያ ጌታነህ የደቡብ አፍሪካን የሊግ ጨዋታ በፍጥነት መላመዱን ነው።
ጌታነህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በበርካታ ጨዋታዎች ያገለገለ ሲሆን፤ ለአዲሱ ክለቡ (ዊትስ ዩኒቨርሲቲ) ሲጫወት በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ኢትዮጵያና ማዕከላዊ አፍሪካ ካደረጉት የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኋላ ለዋሊያዎቹ አልተሰለፈም።
የጌታነህ በጉዳት ምክንያት ቡድኑን አለማገልገል የአጥቂ መስመሩን አዳክሞታል የሚሉ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች የጌታነህን የጤንነት ሁኔታ ከሕክምና ባለሙያዎች ባልተናነሰ መልኩ እየተከታተሉ ናቸው።
«ይህን ወሳኝ አጥቂ በጉዳት ምክንያት ማጣት በጨዋታው ውጤት ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል። በተለይ በነጥብ ጨዋታዎች አጥቂው አገሩን አለማገልገሉ ዋጋ ያስከፍላል» በማለት በርካቶች እየተነጋገሩበት ናቸው።
ይህንንም አዲስ አበባ ላይ ዋሊያዎቹ ከቦትስዋና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ በግልጽ አሳይቷል። ቡድኑ ግብ ማስቆጠር ተስኖት በ89ኛው ደቂቃ ላይ ከ25ሺ በላይ የስታዲ የሙንና በቤቱ ሆኖ ጨዋታውን የሚከታተለውን ተመልካች ያስፈነደቀና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የምድቡ መሪ እንዲሆን ያስቻለበትን ጊዜን እናስታውሳለን።
getahun kebede SAለደቡብ አፍሪካው ቢድቬስት ዊትስ የሚጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ጌታነህ ከበደን የጤንነት ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዶክተር ተረፈ ጣፋ ከነበረበት ጉዳት እያገገመ መሆኑን የቢድቬስት ዊትስ ዶክተር በኢሜል እንደገለጹላቸው ለማወቅ ችለናል።
ዶክተር ተረፈ የዊትሱ ዶክተር ፒላይ ገለጹልኝ እንዳሉት «ከዚህ በፊት ያደርጉለት የነበረውን ዓይነት ሙከራ በማለፉ ዓርብ ዕለት ልምምድ ጀምሯል። ለናይጄሪያ ጨዋታም ሊደርስ የሚችልበት ዕድል ሊኖር ይችላል» በማለት እንደጻፉላቸው ነው ዶክተር ተረፈ የተናገሩት።
«ኮንጎ ብራዛቪል ላይ ከማዕከላዊ አፍሪካ ጋር እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ከናይጄሪያ ጋር ስንጫወት ጌታነህን በማጣታችን ተጎድተናል» በማለት ለዊትሱ የሕክምና ዶክተር መንገራቸውን የገለጹት ዶክተር ተረፈ፤ በየዕለቱ በኢሜል መልዕክት እየተለዋወጡ መሆኑንና የልጁን ጤንነት የዊትሱ የሕክምና ዶክተር እየተከታ ተሉት እንድሆነ ነው ያስረዱት።
በቀጣይ ባሉት ቀናትም የተጫዋቹን ጤንንት በአጽንኦት እንደሚከታተሉና ጌታነህንም አዲስ አበባ ከመምጣቱ በፊት በስልክ ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርጉ የቡድኑ ዶክተር ዶክተር ተረፈ ገልጸዋል።
እንደ ብሔራዊ ቡድኑ ዶክተር ገለጻ፤ ቀለል ያለ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው ምንያህል ተሾመ ከጉዳቱ አገግሞ ከዋሊያዎቹ ጋር ልምምዱን እንደጀመረና ሌሎቹ ተጫዋቾችም በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።


zehabesha

No comments:

Post a Comment