Monday, November 4, 2013

የአሌክስ ፈርጉሰን መጽሐፍ እያነጋገረ ነው


ከዳዊት በጋሻው
በእንግሊዝ እግር ኳስ ገናና ስም የገነቡትና በርካታ ሽልማቶችን ማግኘት የቻሉት የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ቻፕ ማን ፈርጉሰን 26 ዓመታት የማንቸስተር ቆይታ በኋላ በራሳቸው ፈቃድ ከኦልድትራፎርድ መልቀቃቸው ይታወቃል።
ከአሰልጣኝነት መልቀቃቸውን ተከትሎ ከስፖርት ቤተሰቦች እስከ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም እስከ እንግሊዝ ፓርላማ የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ቻፕ ማን ፈርጉሰን ከኦልድትራፎርድ መልቀቅ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ነበር
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች ለእንግሊዝ እግር ኳስ ድምቀት የነበሩት ፈርጉሰን መልቀቃቸው አሳዛኝ ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል። ዳቪድ ካሜሩን የፈርጉሰንን ከአሰልጣኝነት መሰናበት «እንግሊዝ በእግር ኳስ አንድ ሰው አጣች፤ ፈርጉሰን የእግር ኳስ ስኬት ተምሳሌት ናቸው» ሲሉ ገልጸዋቸው ነበር
ቢቢሲ ስፖርት፣ ስካይ ስፖርት፣ አልጀዚራ ስፖርት፣ ሱፐር ስፖርት፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሮይተርስ፣ ማርካ፣ ኪከር፣ ጎል ዶት ኮም፣ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ዋሽንግተን ፖስትና የመሳሰሉት የዓለም ታላላቅ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን የፈርጉሰንን ከማንቸስተር አሰልጣኝነት መልቀቅ በአንድ ድምጽ «ስኬታማው አሰልጣኝ ከአሰል ጣኝነታቸው በራሳቸው ፈቃድ ለቀቁ፤ ላለፉት ዓመታትም በእንግሊዝ እግር ኳስ በጣም ስኬታማው ሰው ነበሩ » ብለዋቸው ነበር

http://www.44prx.cf/browse.php?u=Cy1hnPK7HvFZLXxQzf6ZSX3ODeqJIjS9UuSHfWLlYxL%2Fdw5bdidS%2F6jO0lrxfkw3Q2IRuZs7%2FeMONg3tycDXHdF9MqezAzIBbQ%3D%3D&b=2
ውጤታማው አሰልጣኝ ከኦልድትራፎርድ የለቀቁት ባለፈው ግንቦት 2013/14 የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ የውድድር ዓመት መጠናቀቂያ ላይ ነበር። ፌርጌ ኦልድትራፎርድን የለቀቁት በስኬት ነበር ይኸውም 2013/14 የእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ዋንጫን በማንሳት ነበር።
ያኔ ታዲያ ፈርጉሰንን በመተካት የቀያዮቹ አሰልጣኝ ማን ይሆናል የሚለው በዓለም የመገናኛ ብዙኃን ትልቅ ትኩረት አግኝቶ ነበር። ሌላውን ስኮትላንዳዊና የአገራቸው ልጅ የሆኑትን ዳቪድ ሞይስን እንዲተኳቸው ያደረጉት ፈርጉሰን ከቴአትር ኦፍ ድሪምስ ከተለዩ እነሆ ስድስት ወር ሞላቸው
አሌክስ ፈርጉሰን ከአሰልጣኝነት ለምን እንደለቀቁ በተጠየቁ ጊዜ «የባለቤቴ እህት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቷ፣ ባለቤቴ ብቸኝነት ተሰምቷታል፤ ስለዚህ ከቤተሰቤ ጋር መሆን እሻለሁ» ሲሉ ለስካይ ስፖርት መናገራቸው ይታወሳል
ከአሰልጣኝነታቸው በራሳቸው ፈቃድ ከለቀቁ ከስድስት ወራት በኋላ በስፋት የእግር ኳስ ህይወታቸ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ባለፈው ማክሰኞ አስመርቀዋል።
የፈርጉሰን መጽሐፍ «ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ግለ ታሪክ (ser Alex Ferguson » በሚል ርዕስ የተጻፈው ሲሆን በርካታ እግር ኳሳዊ ክስተቶች እንደተካተቱበት ተነግሯል። በተለይ ከተጫዋቾች ስለ ዳቪድ ቤካም፣ ሮይ ኪን፣ ዋይኔ ሩኒና ክርስቲያኖ ሮናልዶ፤ ከክለቦች ደግሞ ስለ ሊቨርፑልና ማንቸስተር ሲቲ በስፋት እንደሚዘረዝር የእንግሊዙ መገናኛ አውታር ቢቢሲ ከለንደን ዘግቧል
71 ዓመቱ ፈርጉሰን በመጽሐፋቸው ዳቪድ ቤካምን በተመለከት « ዳቪድ በጣም ጎበዝና ታታሪ ተጫዋች ነበር፤ ነገር ግን በኋላ ላይ ይህን ታታሪነቱን አጣንበት፤ እንድያውም ከሪያል ማድሪድ ጋር በሚስጢር እየተደራደረ መሆኑን ሰማን፤ ከነበረው አቋምም በጣም እየወረደ መጣ » በማለት ተናግረዋል።
በተጨማሪም «.. የካቲት 2003 በኤፍ ካፕ ጨዋታ ላይ በአርሴናል 2 0 ስንሸነፍ ሁለተኛዋ ግብ በእርሱ ስህተት ነበር የተቆጠረችው። ዳቪድ ታዲያ ስህተቱን ማመን አልፈለገም ነበር። በመልበሻ ክፍል ውስጥ ሳለን ፞ቡደኑን ንቀኸዋል። የምትፈልገውን አድርግ፞ አልኩት» በማለት በጊዜው የነበራቸውን አለመግባባት በመጽሐፋቸው አስፍረውታል።
ፈርጊ ስለ ቤካምና ስለ እራሳቸው ሲናገሩ «ዴቪድ ቤካም ስህተቱን ማመን ስላልቻለ ከአርሰናል ጋር ያደረግነውን ጨዋታውን በምስል አሳየሁት። ምንም ነገር መናገር አልፈለገም ነበር፤ ምን እያተነጋገርን እንደሆንና ለምንስ ከአንተ ጋር መገናኘት እንደፈለኩ ገብቶሃል አልኩት። መልስ ሊሰጠኝ እንኳን አልፈለገም» ሲሉ ጽፈዋል።
ፈርጊ ቀጥለውም « በሌላኛውም ቀን እኔ ሳናግረው ምንም ምላሽ ሊሰጠኝ አልፈለገም» ታዲያ ያኔ አጠገቤ ያገኘሁትን ጫማ ስወረውረው ቀኝ አይኑ አካባቢ መታሁት በማለት የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከቀያዮቹ ቤት ሊወጣበት ያነሳሳውን ምክንያት በመጽሐፋቸው ጠቅሰውታል።
ፈርጉሰን በመጽሐፋቸው «ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትልቅ ተሰጥኦ ያለው ተጫዋች ነው፤ እርሱን መሸጥ በጣም ያሳዝናል። እርሱን መሸጥ ማለት ራስን መግደል ማለት ነው» በማለት ለፖርቹጋ ላዊው የቀድሞ ኮከባቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል
የቀድሞ የሊቨር ፑል አሰልጣኝ ከነበሩት ስፔናዊው ራፋኤል ቤኔቴዝ ጋር የነበራቸው ቁርሾ የተነሳው ስፔናዊው አሰልጣኝ የሚሰነዝራቸው አስተያየቶች በሙሉ ግለሰባዊ ስለሆኑ መሆኑን ገልጸዋል። እንግሊዝ በቴክኒክ የተካኑ ተጫዋቾች እስከሌላት ድረስ የዓለም ዋንጫን እንደማታሸንፍ በመጽሑፉ ላይ ሽፋን ሰጥተዋል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል
ውጤታማው ፈርጉሰን 26 ዓመታት የኦልድትራፎርድ አሰልጣኝነት ቆይታቸው፣ 13 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ አምስት ኤፍ ካፕ፣ ሁለት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አራት ካርሊን ካፕ (የአሁኑ ሊግ ካፕ) ዋንጫዎችን ማንሳት ችለዋል በአሰልጣኝነታቸውም ዳቪድ ቤካምን ጨምሮ እንደነ ፔተር ሽማይክል ኤሪክ ካንቶና፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ብርያን ሮብሰን፣ ሮይ ኪን፣ ጃፕ ስታም እና ሩድ ቫልኒስትሮይ የመሳሰሉትን ታላላቅ ተጫዋቾች ያሰለጠኑ ሲሆን 38 ሽልማቶችንም ማሸነፍ ችለዋል።
እኒህ አንጋፋ አሰልጣኝ ከአሰልጣኝነት ራሳቸውን ባገለሉ ጊዜ «ወደ ኦልድትራፎርድ መጥተው የማንቸስተርን ጨዋታ ይከታተሉ ይሆን? ተብለው ሲጠየቁ « አይ አላይም » በማለት ቢመልሱም ባለፈው ቅዳሜ ግን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተገኝተው ማንቸስተር ዩናይትድ ከስቶክ ሲቲ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ በኦልድትራፎርድ ተከታትለው ነበር። ጨዋታውንም የቀድሞ ክለባቸው ማንቸስተር ዩናይትድ ሆላንዳዊው ሮቢን ቫንፔርሲ፣ እንግሊዛዊው ዋይኔ ሩኑና ሜክሲኳዊው ሀቪር ሄርናንደዝ ችቻሪቶ ወይም ትንሹ አተር ባስቆጠሯቸው ግቦች 32 ማሸነፍ ችሏል።

zehabesha

No comments:

Post a Comment