ነገሩ ዛሬ ነዉ ለቡድኑ አባላት የተነገረዉ…ነገ በጥዋት ተነስተዉ ወደ ዮርዳኖስ ያቀናሉ፤ከ2ት ቀን በሁዋላ ከኢራቅ አቻቸዉ ጋር በዮርዳኖስ የወዳጅነት ጨዋታ አደርገዉ በማግስቱ እሁድ አዲስ አበባ ይገባሉ፤ዋልያዉ እስካሁን ድረስ የተባሉት የወዳጅነት ጨዋታዎች ሳይቀኑት እነሆ የሩቅ ሀገርዋ ኢራቅ ጋር ተሳክቶለት ይጫወታል፤አብዛኛዉ ወጪ የምግብና ማረፊያን ጨምሮ የዋልያዉ ወጪ የሚሸፈን ይሆናል፤
የመሄዳቸዉ ነገር የረጋገጠ ስለሆነ እንደዚህ ቀደሞቹ ጨዋታዎች ጉንጭ አልፋ አይሆንም፤አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ 23ቱን ተጫወቾቹን ይዘዉ ወደ ዮርዳኖስ ይጓዛሉ፤እነሳላሀዲን አዲስ ሽመልስ እና ጌታነህ ሲመጡ 4ት ተጫወቾችን ይቀንሱና 23 ተጫዋቾን ይዘዉ ወደ ካላባር ያመራሉ ማለት ነዉ፤
በነገራችን ላይ ወደ ኢራቅ የሄደዉ ኢትዮጲያዊ ቡድን ባንክ ነበር፤በኢራቅ ወታደሮች ቡድን 13 ግቦች ዘንቦበት ነበር የተመለሰዉ..ከዛ ወዲህ ወደ ሩቅ ምስራቆቹ ሀገራት የተጓዘዉ ይሀዉ ዋልያ ሲሆን በካታር ከቱኒዚያ ጋር ባለፈዉ አመት መጫዋቱ ይታወሳል፤
ለቡድኑ አባላት ነገ እንደሚሄዱና ጨዋታ እንዳለ ሲነገራቸዉ ሚስጥር ነዉ እንዳትናገሩም ተብለዋል፤እድሜ ለዮርዳኖስ ምንጮቻችን ይሁንና ሚስጥሩ ይፋ ሁንዋል፤ዋልያዉ ከሳዳም ሁሴን ሀገር ጋር ይጫዋታል ማለት ነዉ፤አደራ ግን ለማንም እንዳታወሩ..
http://www.ethiotube.net
No comments:
Post a Comment